መደበኛ ያልሆነ

ሀምሌ 5፤2015-ሰሜን ኮሪያ አሜሪካን ካስፈራራች በኋላ አህጉር ተሻጋሪ ባልስቲክ ሚሳኤል ተኮሰች

ሰሜን ኮሪያ አህጉር ተሻጋሪ ባልስቲክ ሚሳኤል (ICBM) መተኮሷን የጃፓን መንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል። የረዥም ርቀት ሚሳኤሉ ከአንድ ሰአት በላይ በአየር ላይ ቆይታ ያስቆጠረ ሲሆን በጃፓን ውሃማ አካል ላይ ይወድቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የጃፓን የመከላከያ ሚኒስትር ተናግረዋል።

ሰሜን ኮርያ ይህንን እርምጃ የወሰደችው የአሜሪካ የስለላ አውሮፕላኖች ወደ ግዛቴ ገብተዋል በሚል አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ከዛተች በኋላ ነው። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ እንደነዚህ ያሉትን አውሮፕላኖች መትቶ እንደሚጥል የሰሜን ኮርያ መንግስት ዝቶ ነበር።

ዋሽንግተን የወሰድኩት ወታደራዊ እርምጃ ከአለም አቀፍ ህግ ጋር የተጣጣመ ነው ስትል ክሱን ውድቅ አድርጋለች። በዛሬው እለት፣ የጃፓን እና የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ሚሳኤሉ መወንጨፉ መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ሁለቱም ሀገራት ሚሳኤሉ አይሲቢኤም ወይም አህጉራትን የሚያቋርጥ የረጅም ርቀት ሚሳኤል ነው ተብሎ ይታመናል ብለዋል።

ይህው ሚሳኤል በተለይም ከሰሜን ኮርያ በመነሳት የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶችን የመምታት አቅም አለው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *