በጎፋ ዞን ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በገዜ ጎፋ ወረዳ የአላ ጋልጣ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ለአርሶ አደሩ የገባ 130 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ዩሪያ እና ዳፕ በህገ-ወጥ መንገድ ሽጠውት በእንቅስቃሴ ላይ መያዙ ተነግሯል ።
የቀበሌው የግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ታረቀኝ ኡንደ የሚባል ሲሆን ነዋሪነታቸው በጉራጌ ዞን ለሆነ አራት ግለሰቦች በመሸጥ በሲኖትራክ ተሸከርካሪ አስጭነው እንደሸኑ መረጋገጡን የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አ/ቶ ካሳሁን አባይነህ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ። ግለሰቡ 449 ሺ ብር እጅ በእጅ በመቀበል አስጭነው ሲሸኝ ለዞኑ ፖሊስ መምሪያ በደረሰ ጥቆማ በሣውላ ከተማ መግቢያ ተጠርጣሪዎችን ከተሽከርካሪው ጋር ከምሽቱ ሰባት ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል ።
ከተያዙ በኋላ መርማሪ ፖሊስ የተጠርጣሪዎችን ቃል የተቀበለ ሲሆን ተጠሪጣሪዎች ለቀበሌው ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ታረቀኝ ኡንደ በእጅ 449 ሺህ ብር በመስጠት ቀሪውን 100 ሺህ ብር በሞባይል ባንክንግ የሰጡት ሲሆን በአጠቃላይ 549 ሺ ብር የከፈሉ መሆኑን አረጋግጠዋል ።
በአበረ ስሜነህ