መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 10፤2015-በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ ???? አራት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ እሁድ ሀምሌ 9 ቀን ከምሽቱ ሶስት ሰዓት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት እና ቁጥጥር ዲቪዥን ኢንስፔክተር ታደሰ ውሪሳ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 89883 ኢቲ የሆነ ተሸከርካሪ የእርሻ ማዳበበሪያ ጭኖ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረማርቆስ ሲጓዝ ከአዲስ አበባ 135 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ አሊዶሮ ቀበሌ ወረቤ የተባለ አካባቢ 5 ተሸከርዎችን በመግጨት ባደረሰው ጉዳት የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጸዋል፡፡

ኮድ 3 ኦሮ 33556 የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ 16 ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ ከሱሉልታ ወደ ጎሃጽዮን ሲጎዝ ሙሉ ለሙሉ ተሸከርካሪው ላይ የወጣበት ሲሆን ከተሳፋሪዎች መካከል፣ ከአንድ ቤተሰብን አምስት ሰዎች ጨምሮ ረዳት እና ተሸከርካሪውን በአጠቃላይ 14 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል አራት ተሸከርካሪዎችን በመግጨት በተለምዶ ዶልፊን ከሚባለዉ ተሸከርካሪ ውጪ የከባድ መኪናው አሽከርካሪዉን ጨምሮ አራት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ አደጋው ከፍተኛ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን አሽከርካሪዎች ከወቅቱ የአየር ሁኔታ ጋር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኢንስፔክተር ታደሰ ውሪሳ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *