መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 10፤2015-ችግኝ መትከላችንን በጠዋት ጀምረናል፣ እስከምሽት ይቀጥላል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ ማለዳ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
በማለዳ በዝናብ ወጥታችሁ አረንጓዴ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ ለምትገኙ ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ምስጋናችን ይድረስ ብለዋል።

ዛሬ ኢትዮጵያውያን በህብረት ታሪክ የምንሰራበት ቀን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ÷ ዛሬ ለእኛ ቀላል የሚመስለው ጉዳይ ብዙዎች የከበዳቸው እና የማይችሉት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ሕጻናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሃገራቸውን አረንጓዴ አልብሰው ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ መቁረጣቸው ትልቅ መታደል መሆኑንም ገልፀዋል።

በጠዋት ጀምረናል፤ እስከ ምሽት መትከላችን ይቀጥላል፣ በርቱ፣ በዝናብ የቆምነው የተሻለ ሀገር ለመፍጠር ነው ሲሉ አክለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *