መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 17፤2015-የስፔን ወግ አጥባቂው ፓርቲ በምርጫ ሁለንተናዊ ድል ማግኘት እንዳልቻለ ተነገረ

በስፔን በትላንትናው እለት በተደረገው ብሄራዊ ምርጫ የቀኝ እና ግራ ዘመም ፓርቲዎች አዲስ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ግልፅ ውጤት ሳይኖራቸው ወደ ህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት ለማምራት ተገደዋል። እሁድ እለት 99 በመቶ የመራጮች ድምፅ የተቆጠረ ሲሆን የወግ አጥባቂው ተቃዋሚው ህዝቦች ፓርቲ ወይም (PP) 136 መቀመጫዎችን በምክር ቤቱ ውስጥ ሲያገኝየጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ገዥው የሶሻሊስት ሰራተኞች ፓርቲ ደግሞ 122 መቀመጫዎች በምክር ቤቱ ውስጥ አሸንፏል።

በምርጫው አነስተኛ መቀመጫን በምክር ቤቱ ያገኙ ሁለት ፓርቲዎች በሚሰጡት ድጋፍ የምርጫውን መልክ ሊቀይር እንደሚችል ተጠቁሟል።33 መቀመጫዎች የቀኝ ዘመሙ ቮክስ ፓርቲ ያገኘ ሲሆን ግራ ዘመሙ ሱማር ደግሞ 31 መቀመጫን አግኝቷል።

ሶሻሊስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ 99 በመቶ የሚሆነው የመራጮች ድምፅ ከተቆጠረ በኃላ የግራ ዘመም ኃይሎች የቀኝ ክንፉ ማሸነፋቸውን ገልፀዋል። ምንም እንኳን መንግስት ለመመስረት የሚያስችል መተማመኛ ድምፅ ባያገኙም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ይህንኑ ተናግረዋል። “ባለፉት አራት አመታት ያስመዘገብናቸው እድገቶች በሙሉ ወደ ኋላ ሊጎትት የሞከረው ቡድን ከሽፏል” ሲሉ ሳንቼዝ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *