መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 17፤2015-ዩክሬን በሞስኮ የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ፈፅማለች ስትል ሩሲያ ከሰሰች

ዛሬ ማለዳ በሞስኮ ከተማ ቢያንስ ሁለት ሕንፃዎች ላይ ጉዳት ካደረሰው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ጀርባ ዩክሬንን እጅ አለበት  ስትል ሩሲያ ከሳለች። የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች “በሞስኮ ተከስክሰዋል” ሲል ገልጿል።

የሩሲያ መንግስታዊ የዜና ወኪል የሆነው ታስ እንደዘገበው አንድ ሰው አልባ አውሮፕላን ከመከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አቅራቢያ ወድቋል።የዩክሬን ባለስልጣናት በጥቃቱ ዙሪያ እስካሁን ዝምታን የመረጡ ሲሆን በሩሲያ ላይ ለሚሰነዘሩት ጥቃቶች ሃላፊነቱን ከመውሰድ ሲቆጠቡ ይስተዋላል።

የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጌይ ሶቢያኒን እንደተናገሩት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቱ “መኖሪያ ባልሆኑ” ሕንፃዎች ላይ ዛሬ ማለዳ ደርሷል። ህንፃዎቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸውም አክለዋል።

የሩስያ አየር መከላከያ ሃይሎች በሞስኮ ላይ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃትን ከአየር ለይ ማውረዱን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኪየቭ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ላይ “የሽብር ድርጊት” ጀምራለ ሲል ከሰሰ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *