መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 21፤2015-የናይጄሪያ ኮሜዲያን የፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበሱ ወቀሳ ቀረበበት

ታዋቂው ናይጄሪያዊ ኮሜዲያን አብዱልጋፋር አቢዮላ ወይም ኩቴ አቢዮላ በመባል የሚታወቀው ግለዘብ የፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበሱ ችግር ውስጥ ገብቷል።

ኮሜዲያኑ በፖሊስ እየተመረመረ ሲሆን “የፖሊስ የደንብ ልብስን ለብሶ ክብር የጎደለው እና የሚያንቋሽሽ ስራ ሰርቷል” በሚል ክስ ሊመሰረትበት ይችላል።የፖሊስ ቃል አቀባይ ኦሉሙዪዋ አዴጆቢ በትዊተር ገፃቸው በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሉት “ህጉ አንድ ግለሰብ በማንኛውም መልኩ የፖሊስ ተቋሙን በሚያጠለሽ መልኩ  የደንብ ልብስ አጠቃቀምን በሚመለከት የወጣውን ድንጋጌ እንዳይጥስ ይከለክላል።

ኮሜዲያኑ ባለፎ ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ያጋራቸዉ ሁለት ምስሎች የናይጄሪያን ፖሊስ አስቆጥቷል፡፡አንደኛው ኮሜዲያን እንደ ፖሊስ አባል ለብሶ አንድ ሞተረኛን የፖሊስ መኪናዉ ቤንዚን ስለጨረሸ ለመኪና ነዳጅ ገንዘብ እንዲሰጠው ሲጠይቀው ያሳያል። ይህም የናይጄሪያን ፖሊስ በጉቦ እንዲሳል ማድረጉን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።

የፖሊስ ቃል አቀባዩ ሌሎች ግለሰቦችም ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል፡፡ የፖሊስ ኃይል የደንብ ልብሱን  ክብር ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑንም አስታዉቋል፡፡

ማንኛውም ግለሰብ ሆነ አካልበፖሊስ የደንብ ልብስ ላይ ወይም በሚወክለው ተቋም ላይ የስም ማጥፋት ድርጊትን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ይሰራል። ” በማለት ተናግረዋል።

ኮሜዲያኑ ከፖሊስ ጋር እንዲህ ዓይነት ችግር ዉስጥ ሲገባ የመጀመሪያዉ አይደለም፡፡በ2021 ዓመት የባህር ኃይል መኮንን ሆኖ ሲሰራ የወታደሩን የማህበራዊ ሚዲያ ፖሊሲ በመጣሱ በቁጥጥር ስር ዉሎ ነበር፡፡ባለፈው አመት ከሰራዊቱ በይፋ ራሱን አገሏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *