መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 25፤2015-ጦርነቱ ወደ ሩሲያ እየተመለሰ ነው ሲሉ ዘለንስኪ ተናገሩ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ በሰጡት መግለጫ ጦርነቱ ወደ ሩሲያ እየተመለሰ መሆኑን አስጠንቅቀዋል። ዘሌንስኪ በሩሲያ ግዛት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚካሄደው ጦርነት የማይቀር፣ ተፈጥሯዊ እና ፍፁም ፍትሃዊ ሂደት ነው ብለዋል።

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው እሁድ እለት ሶስት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች መትቶ መጣሉን ያስታወቀ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሁለቱ በመስሪያ ቤት ህንፃ ላይ ወድቀዋል ሲል አስታውቋል። ከከተማው መሀል ደቡብ ምዕራብ የሚገኘው ቭኑኮቮ አውሮፕላን ማረፊያ ለአጭር ጊዜ ተዘግቷል። እሑድ ረፋድ ላይ የተፈጸመው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ሞስኮ የኪዬቭ ስራ ነው ስትል ወንጅላለች።

የሩሲያ የጦር አመራሮች ለሁለት ሳምንታት ብቻ ይቆያል ብለው ያሰቡት የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ‘ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” 522ኛ ቀኑን ዛሬ አስቆጥሯል። “ቀስ በቀስ ጦርነቱ ወደ ሩሲያ ግዛት  ወደ ተምሳሌታዊ ማዕከሎች እና ወታደራዊ ማዕከሎች እየተመለሰ ነው እና ይህ የማይቀር ተፈጥሯዊ እና ፍፁም ፍትሃዊ ሂደት ነው ሲሉ ዘለንስኪ የጦርነቱን መነሻ በመግለፅ አብራርተዋል።

የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ እንደተናገሩት የዩክሬን ቀጣይነት ያለው የመልሶ ማጥቃት የተሳካ ከሆነ ሞስኮ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መጠቀም አለባት ሲሉ ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *