መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 26፤2015-በአሜሪካ አንዲት እናት ክርስቶስ ወደ ምድር በቶሎ ለፍርድ እንዲመጣ በሚል ሁለት ልጆቿን ገደለች

በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት እናት በአፖካሊፕቲክ ሃይማኖታዊ እምነቷ መሰረት ሁለት ልጆቿን በመግደል እና የባሏን የቀድሞ ሚስት ለመግደል በማሴር የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባታል።ሎሪ ቫሎው የተባለችዉ ይህችዉ ሴት በግንቦት ወር የ16 ዓመቷን ሴት ልጇን ታይሊ ራያን  እና የሰባት ዓመት በማደጎ የወሰደችዉን ወንድ ልጇን ኢያሱ “ጄጄ” ቫሎውን በመግደል ጥፋተኛ ተብላለች፡፡

የእናታችን ኃጢአት (Sins of Our Mother) በሚል የዚህችዉ ሴት የህይወት ታሪክ በኔትፍሊክስ እውነተኛ የወንጀል ዘጋቢ ፊልም የቀረበ ሲሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምጽዓት እንዲሆን ልጆቿን መግደሏ ከአምላክ የተሰጠ ራዕይ መሆኑን ትናገራለች፡፡

ዳኛ ስቲቨን ደብሊው ቦይስ በቫሎው የወንጀል ድርጊት ላይ ባሳለፉት የጥፋተኛነት ዉሳኔ በሶስት ተከታታይ የእድሜ ልክ እስራት በይነዋል፡፡ በወላጅ የተፈጸመውን የልጅ ግድያ “በእርግጥ መገመት ከምችለው በላይ አስደንጋጭ ነገር” ሲሉ ዳኛዉ ገልጸዋል።

ቫሎው ልጆቿን ከገደለች በኃላ እንኳን እንደጠፉ ገልጻ ባታዉቅም በፖሊስ አስክሬናቸዉ ተገኝቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *