መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 26፤2015-አዲስ አበባ ከተማ ላይ የተሰረቀዉ ተሽከርካሪ በሻሸመኔ መገኘቱ ተነገረ

አዲስአበባ ከተማ ጨርቆስ አካባቢ ሐምሌ 11 ቀን 5L ሚኒባስ ተሽከርካሪ ለጥገና ስራ በጋራዥ ዉስጥ ከቆመበት የተሰረቀ ሲሆን ተሽከርካሪዉ ከቀናት በኋላ በሻሸመኔ ከተማ ቀበሌ 04 ቀበሌ ላይ መገኘቱን የአሽከርካሪዉ ባለቤቶ አቶ ወንድሜነህ ለብስራት ራዲዮ እና ቴቪ ተናግረዋል።

ግለሰቡ አመታትን በዉጭ ሀገር ከባለቤታቸዉ ጋር በመሆን ሰርተዉ የገዙት መኪና ሶስት ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበት እንደነበር ገልፀው በእለቱ መሰረቁን ለጣቢያችን ገልጸዉ ነበር።

የግለሰቡ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ አወሊያ ሽኩር እንደተናገሩት በእለቱ ከሌሊቱ 6 ሰዓት የመኪናቸዉን መሰረቅ እንደሰሙ ተናግረዋል። በኋላም ጨርቆስ አካባቢ ከሚገኘዉ ጋራዥ ተሰርቆ የጠፋዉ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በመጀመሪያ ወደ ቢሾፍቱ ከተማ እንዲሸሽ አድርገዉ እንደነበር ተጎጂዎቹ ገልጸዋል። በመቀጠለም ለሶስተኛ አካል በመሸጥ ገዢዉ ተሽከርካሪዉን ወደ ሻሸመኔ ከተማ ይወስደዋል። በዛም ከአንደ ወዳጁ መኖሪያቤት ይሸሽገዋል።

ተሽከርካሪዉ ከጠፋ ከ 11 ቀናት በኋላም በፖሊስ አባላት ፍለጋ ሊገኝ መቻሉን አቶ ወንድሜነህ ጠቁመዋል። ተሽከርካሪዉ በተገኘነት ወቅትም የተለያዩ ልዩ መለያዎቹ እንደጠፉ ተናግረዋል።

ከተሽከርካሪዉ ስርቆት ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት ቁጥራቸው ከ 5 በላይ የሆኑ ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸዉንም ወ/ሮ አወሊያ ተናግረዋል።

ግለሰቦቹ ለመኪናቸዉ መገኘት ለተባበሯቸዉ የህግ አካላት ፣ ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ እንዲሁም ለብስራት ራዲዮ እና ቴቪ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *