መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 26፤2015-የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ለሴት ልጃቸው ከፍተኛ ሹመት ሰጡ

???? ፕሬዝዳንቱ ለሶስት ልጆቻቸው ስልጣን ሰጥተዋል

የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ሴት ልጃቸውን በቢሯቸው ውስጥ ቁልፍ ቦታ ላይ ሾመዋል። የ29 ዓመቷ አንጌ ካጋሜ የስትራቴጂ እና የፖሊሲ ምክር ቤት ሀላፊ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾሟን ፕሬዝዳንት ካጋሜ የመሩት የካቢኔ ስብሰባ ማክሰኞ እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በመግለጫው በኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ፣ ግብፅ እና ጊኒ አዳዲስ አምባሳደሮችን ጨምሮ ሌሎች ሹመቶችን ይፋ አድርጓል። የካጋሜ ሴት ልጅ ከ 2019 ጀምሮ በፕሬዚዳንት ቢሮ ውስጥ በከፍተኛ የፖሊሲ ተንታኝ ሆነና በመስራት ላይ ትገኛለች።

ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የፖለቲካ ሳይንስ እና የአለም አቀፍ ጉዳዮች ዲግሪን አግኝታለች። ሌሎች ሁለት የፕሬዚዳንት ካጋሜ ልጆች በመንግስት ስልጣን ውስጥ ቦታ ይዘዋል።

የበኩር ልጃቸው ኢቫን ካጋሜ እ.ኤ.አ. በ2020 የሩዋንዳ ልማት ቦርድ ሰብሳቢ ተደርገው የተሾመ ሲሆን በግሉ ዘርፍ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትን የማስመዝገብ ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ሦስተኛው ልጃቸው ኢያን የሩዋንዳ መከላከያ ኃይል መኮንን ሲሆን ባለፈው ዓመት በፕሬዚዳንቱ ጠባቂነት ተመድበዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *