መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 28፤2015-በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተያዘ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የፖሊስ አባላት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ወቅት ከነ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የጨፌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት በወረዳ 11 በተለምዶ ፀበል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለፀጥታ ስራ ሲባል ትናንት ሃምሌ 27 ቀን 2015 ዓ/ም ምሽት ድንገተኛ ፍተሻ አድርገው ነበር ሲል የአዲስአበባ ፖሊስ አሳዉቋል፡፡

በታክሲ ተሳፍሮ እየተጓዘ የነበረ አንድ ግለሰብ በተጠቀሰው ቦታ ላይ ሲደርስ ፍተሻ መኖሩን በማወቁ ከታክሲው ወርዶ በእግሩ መጓዝ ይጀምራል፡፡ ነገር ግን ፍተሻው ቦታ ላይ ሲደርስ ለምን ወርዶ መሄድ እንደፈለገ የተጠራጠሩ የፖሊስ አባላት ተከታትለው ያስቆሙታል፡፡

በእጁ የያዘውን ፌስታል ሲፈትሹ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር አግኝተው ከነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር አውለውታል መባሉን ብስራት ራዲዮ እና ቴቪ ሰምቷል፡፡ በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገም ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *