መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 1፤2015-በኬንያ በአረጋውያን መንከባከቢያ ስፍራ አንዲት አዛውንት በሸንኮራ አገዳ ሲገረፉ መታየቱ ቁጣን ቀሰቀሰ

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ አቅራቢያ በሚገኝ የአረጋውያን ማቆያ ቤት ለአደጋ የተጋለጡ ነዋሪዎች ላይ እንግልት እና ችላ እንደተባሉ የሚያሳይ መረጃ በምርመራ ተረጋግጧል። በሚስጥራዊ ቀረጻ እንደተረጋገጠው የአረጋውያን መንከባከብያ ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች ላይ ነዋሪዎች አካላዊ እንግልት ሲፈጽሙ፣ ምንም ሳህን በሌለበት ጠረጴዛ ላይ ምግብ በማስቀመጥ እንዲበሉ ማስገደድ እና የጤና እክል የገጠማቸው አረጋውያን ሳይታከሙ ሲጉሏሉ ያሳያል።

ከናይሮቢ በስተ ምዕራብ 20 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የፕሬስባይቴሪያን ቤተክርስቲያን የምስራቅ አፍሪካ ማዕከል ውስጥ ከኃላዋ ምቷት ሲል አንድ ሰራተኛ ሲናገርም የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል። በድብቅ ቀረጻው ሶስት ሐምራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ ግለሰቡች አንዲት በእድሜ የገፉ ግለሰብ ሲያመናጭቁ ታይተዋል።

እኚህ አዛውንት ሲጠሩ ለምን አልመጡም በሚል በሸንኮራ አገዳ ሲገረፉ ይታያሉ ኧረ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ ሲሉም ይደመጣሉ። የአረጋውያን የእንክብካቤ ቤቱ የተቋቋመው በአካባቢው በሚገኝ የቤተክርስትያን የሴቶች ማህበር ሲሆን አሁን ግን ራሱን ችሎ የሚተዳደር ነው። ወደ 50 የሚጠጉ አረጋውያን ሴቶች እና ወንዶች መኖሪያ ነው።

በናይሮቢ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ የአረጋውያን መኖሪያ ቤቶች ቁጥር በሦስት እጥፍ ገደማ ማደጉ ተመዝግቧል።በርካታ የአረጋውያን የማቆያ ስፍራ የቤት ኪራይ አይከፍሉም እንዲሁም በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መዋጮ ይደገፋሉ።

በሚቀጥሉት 30 ዓመታት የአፍሪካ አረጋውያን ቁጥር ከ75 ሚሊዮን ወደ 235 ሚሊዮን በሦስት እጥፍ ይጨምራል ሲል የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ በ2020 ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። እድገቱ ከየትኛውም የአለም ክፍል የበለጠ ፈጣን ይሆናል። ይህም አረጋውያን ዘመዶቻቸውን ሰዎሽ ወደ እንክብካቤ ማዕከላይ የመላክ እድል እየጨመረ እንደሚሄድ ይጠበቃል።

ታዲያ እንዚሁ የመንከባከቢያ ማዕከላት ለአረጋውያን ክብር እንዲሰጡ ማድረግ ካልተቻለ ቀጣዩን ጊዜ ይበልጥ ፈታኝ ያደርገዋል።ይህው ማዕከል በእንዲህ ዓይነቱ መረጃ ከመጋለጡ በፊት የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ የሚሰጡትን አገልግሎት ሰላማዊ ገነት ሲሉ በመገናኛ ብዙሃን ገልፀው ነበር።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *