በኦሮሚያ ክልል 2015 ዓ.ም በሀምሌ ወር የመጨረሻ ሳምንት ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ4 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር እና ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር በላቸው ትኪ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
አደጋዎቹ በሸዋ ቦረሩ ሜዳ፣ገዳ አሳሳ ፣ምስራቅ ሀረርጌ፣ሰሜን ሸዋ፣ሸገር ሲቲ፣ ምዕራብ ቦረና እና ሸዋ ከተማ የደረሱ ናቸው።
የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የቀነሰ ሲሆን ፤ መንስኤዎቹ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣በቂ እረፍት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር እንዲሁም አሽከርካሪዎች እርስ በእርስ በመሽቀዳደም መሆኑን ኮማንደር በላቸው ትኪ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ኮማንደሩ ሲቀጥሉ ሁሉም አደጋዎች በአሽከርካሪዎች ስህተት የተከሰቱ መሆናቸዉን በመግለፅ በተለይም በሸገር ከተማ የተከሰተዉ አደጋ ለ 8 ሰዎች መሞት ምክንያት በመሆን ባለፈዉ ሳምንት ከተመዘገቡ አደጋዎች ከፍትኛዉን ድርሻ ይወስዳል ብለዋል፡፡
በአብርሃም ፍቅሬ