መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 3፤2015-በኬፕ ታውን የታክሲ አድማ ከፍተኛ ትርምስና ሁከት አስነሳ

???? የደቡብ አፍሪካ መንግስት ያወጣውን አዲስ ህግ ከተቃውሞ በኃላ ቀልብሷል

በደቡብ አፍሪካ ዌስተርን ኬፕ ግዛት በኬፕ ታውን ከተማ የታክሲ አገልግሎት መቆም ዜጎችን ለሞት የሚዳርግ ሁከት ያስከተለ ሲሆን የታክሲዎችን አድማ ለማስቆም ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የግዛቱ አስተዳደር አስታውቋል። የስራ ማቆም አድማው ባለፈው ሳምንት ሃሙስ ከጀመረ በኋላ ቢያንስ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

አንዳንድ የኬፕ ታውን መንገዶች የተዘጉ ሲሆን ከከተማዋ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ የሚያደርሱ መንገዶች ተጎድተዋል። በከተማዋ አዲስ የመተዳደሪያ ደንብ መውጣቱ ለአድማው ምክንያት ሆኗል።ከመጠን በላይ የሚጭኑ ታክሲዎችን የመውረስ ስልጣን ለመንግስት የሚሰጥ መሆኑን በደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ የታክሲ ምክር ቤት አስታውቋል።

በተፈጠረው አድማ የማዘጋጃ ቤት አውቶቡሶች የተቃጠሉ ሲሆን የመንግስት ንብረት በጥቃቱ ኢላማ መደረጉን የደቡብ አፍሪካ ራዲዮ ጃካራንዳ ኤፍ ኤም ዘግቧል። የዌስተርን ኬፕ ግዛት ገዢ አለን ዊንዴ ከታክሲ ምክር ቤት ጋር የጋራ ስብሰባ ቢካሄድም ችግሩን ለመፍታት ምንም መሻሻል አልታየም ብለዋል።

በአድማው ምክንያት ነዋሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ወይም ወደ ሥራ፣ ትምህርት ቤት፣ ሱቆች፣ ክሊኒኮች እና ሌሎች ወሳኝ ቦታዎች መሄድ ባለመቻላቸው ተናድጃለሁ” ሲሉ አለን ዊንዴ  ለጃካራንዳ ኤፍ ኤም ተናግረዋል። ባለፉት ጥቂት ቀናት የደረሰውን ሁከት እና የንብረት ውድመት እንዲሁም የህይወት መጥፋት ስናስተውል በታላቅ ሀዘን እና ፀፀት ነው ሲሉ ገዢው ተናግረዋል።

ትላንትን ከሰዓት ዘግይቶ በወጣ መረጃ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ያወጣውን አዲስ ህግ ከተቃውሞ በኃላ ቀልብሷል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *