መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 8፤2015-በበአሜሪካ አንዲት እናት የሰባት ወር ልጇን ለቅሶ ለማስቆም የአልኮል መጠጥ በጡጦ በመስጠቷ ክስ ተመሰረተባት

አንዲት አሜሪካዊት ግለስብ የሰባት ወር እድሜ ያለው ልጇ ማልቀሱን እንዲያቆም  የአልኮል መጠጥ ሰጥታዋለች። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃ እንደዘገቡት ከሆነ ሃኔስቲ ዴ ላ ቶሬ የምትባለ የ37 አመት እናት ህጻን ልጇን ማልቀሱን ለማስቆም በጡጦ ውስጥ መጠጡን ሰጥታዋለች።

ድርጊቱ ከሎስ አንጀለስ በስተምስራቃዊ ክፍል ወጣ ብሎ በሚገኝ አካባቢ የተፈፀመ ሲሆን 55 ህፃኑ  ማልቀስ እንዲያቆም መጠጥ ብትሰጠውም የስካር ምልክት እንደታየበት ተገልጿል።ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ቶሬ ከክስተቱ በኋላ “በልጆች ላይ አደጋ በማድረስ” በሚል ወንጀል ክስ እንደተመሰረተባት የሳን በርናርዲኖ ካውንቲ የአቃቢ ህግ መምሪያ አስታውቋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *