መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 8፤2015-ከ75ሺ በላይ ስደተኞች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል ተባለ

???? ከዚህ ውስጥ ከ 35 ሺ በላይ የሚሆኑት ስደተኞች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸው ተነግሯል

በቅርቡ በአማራ ክልል የተካሄደው ጦርነት ከሱዳን ዋና መግቢያ ወደሆነችው መተማ ሰብዓዊ ተደራሽነትን ውስብስብ እና ፈታኝ እንዳደረገው የዓለሞ የፍልሰተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም አስታውቋል።

በጎንደር መተማ ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ እና በጋምቤላ ክልሎች በተለያዩ የድንበር ማቋረጫ መንገዶች እስካሁን የተመዘገቡ ከ 75ሺ በላይ ስደተኞች መግባታቸው ተነግራል።

የዓለም የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን በላከው መግለጫ 75 ሺህ በላይ ከሆኑት ስደተኞች ዉስጥ 35 ሺህ 623 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከ25 ሺ የሚሆኑት ደግሞ ሱዳናውያን መሆናቸዉን ገልጿል። ቀሪ  የሌላ አገር ስደተኞች መኖራቸዉንም ተቋሙ ለጣቢያችን የላከዉ መግለጫ ያመላክታል።

በተጨማሪም ስደተኞቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት በኩል ድንገተኛ ህክምና ፣ የትራንስፓርት ፣ የንፁ ውሃ መጠጥ አቅርቦትና እና የጤና ልየታ ስራ እየሰራ መሆኑን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *