
ሶማሊያ የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ በሆኑት ቲክቶክ እና ቴሌግራም እንዲሁም ዉርርድ የሚደረግበትን ዋን ኤክስ ቤታ ላይ እገዳ መጣሏን አስታዉቃለችለለ
የሶማሊያ መንግስት እነዚህ መድረኮች “በአሸባሪዎች የሚዘወሩና እና ብልግናን ለማስፋፋት በሚሰሩ ቡድኖች እጅ ስር በመዉደቃቸዉ ወሲብ ፎቶዎችን በማሰራጨት እና ህብረተሰቡን ለማሳሳት እየተጠቀሙበት ነው ብሏል።ሶማሊያ አሁንም ሰፋፊ ግዛቶችን የተቆጣጠረውን የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን በሚቀጥሉት አምስት ወራት ውስጥ ለመደምሰስ ትልቅ እቅድ እንዳላት ስታስታውቅ ነበር።
የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች እገዳውን እስከ ነሀሴ 24 ድረስ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ማድረግ ሳይችሉ ከቀረ ግን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸዉ የመገናኛ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ አስታውቋል።
በቅርቡ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የኢንተርኔት እና የማህበራዊ ሚዲያ ደህንነትን የተመለከተ ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡ይህዉ የኦንላይን መድረክ በወጣቶች ላይ የሚያደርሰዉን አሉታዊ ተፅእኖ አጉልቶ አሳይቷል፡፡ ከነዚህም መካከል “አንዳንዶቹ ህይወታቸውን እንዲያጡ ማድረጉን” ጨምሮ በመድረኩ ተነግሯል።
በሌላ ዜና በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ፖሊስ የቀድሞ የጦር መኮንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ የተቀሰቀሰዉን ተቃውሞ ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙ ተሰምቷል፡፡
በስምኦን ደረጄ