መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 16፤2015-በአሸንዳ ኮንሰርት ከ150 ሺ በላይ ደብተር ለማሰባሰብ እቅድ ተያዘ

በኮሮና  ቫይረስ ወረርሽኝ እና በሰሜኑ ጦርነት ተቆርጦ የነበረው የአሸንዳ ኮንሰርት የፊታችን ነሐሴ 18 በሚልንየም አዳራሽ እንደሚካሄድ  የፕሮግራሙ አዘጋጆች  ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው የፊደል  ላውንጅ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  ተናግረዋል። ኮንሰርቱ በመጀመሪያ ነሐሴ 16 ለማካሄድ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ተመሳሳይ ዝግጅት በመቐሌ ከተማ በመኖሩ ወደ ነሐሴ 18 ሊዞር ችሏል።

ኮንሰርቱን የሚታደሙ  ሰዎች  በዓሉን የሚያሳይ  ባህላዊ ልብሶች ለብሰው እንዲመጡና  በትግራይ  ለተቸገሩና ወላጆቻቸውን በጦርነት ላጡ ህፃናት የሚሆን  የትምህርት ቁሳቁስ ይዘው እንዲመጡ  አዘጋጆቹ  ተናግረዋል።
እስከ 150,00  ደብተር በኮንሰርቱ ላይ  ለመሰብሰብ ታቅዷል።

ከ 25 በላይ የትግረኛ አርቲስቶች የሚሳተፉ ሲሆን  መግቢያው  950 ብር ሲሆን ቪአይ ፒ መግቢያው ደግሞ 2,950 ብር እንደሆነ ተናግረዋል።

ከኮንሰርቱ ከሚገኘው  ገቢ  ላይ በትግራይ  ለሚሰራው የማህበራዊ ስራ ይሰጣል የተባለ ሲሆን ከአምስት አመት በላይ የሆነ ሰው ኮንሰርቱን መታደም ይችላል ተብሏል።

ከመንግስት የፀጥታ ሰራተኞች ባሻገር 120 የደህንነት አካላት ኮንሰርቱ በፀጥታ እንዲከናዉን  ይሰማራሉ ተብሏል።

አዘጋጆቹ ሚልንየም አዳራሽን ነሐሴ 18  ይዞ የነበረው “መርካቶን  በሚልንየም ” የተሰኘው የንግድ ባዛር  አዘጋጆች  ቦታውን  ስለፈቀዱላቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በቤዛዊት አራጌ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *