
ህንድ በዛሬው እለት ሶስተኛ የጨረቃ ተልእኮዋን ለማድረግ የተዘጋጀች ሲሆን ታሪክ ለመስራት እየጠበቀች ትገኛለች። ቻንድራያን 3 የሚል ስያሜ የተሰጠው የጨረቃ ጉዞ ከተሳካ፣ ህንድ በጨረቃ ላይ ብዙ ምርምር ባልተደረገበት የደቡብ ዋልታ አጠገብ በማረፍ የመጀመሪያዋ ሀገር ትሆናለች።
የዚህ የጨረቃ ጉዞ ዋና ዋና ግቦቹ ውስጥ አንዱ በውሃ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ሳይንቲስቶች ወደፊት የሰው ልጅ በጨረቃ ላይ እንዲኖር ይረዳል ላሉት ምርምር ፍንጭ ይሰጣል። የሕንድ የጨረቃ ጉዞ የተደረገው የሩሲያው ሉና-25 በተመሳሳይ የጨረቃን የደቡብ ዋልታ ለመንካት ሲሞክር ከተከሰከሰ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
የህንድ የጨረቃ ጉዞ ከተሳካ አራተኛዋ የዓለም ሀገር ትሆናለች ።አሜሪካ ፣ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት እና ቻይና ሁሉም ከጨረቃ ወገብ አካባቢ ላይ አርፈዋል።ህንድ እ.ኤ.አ. በ2019 የቻንድራያን-2 ተልእኮዋን በደቡብ ዋልታ አቅራቢያ ለማረፍ ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም ። በጨረቃ ወለል ላይ ወድቋል። ስለዚህ አሁን ሁሉም ዓይኖች በቻንድራያን-3 ላይ ናቸው።
በስምኦን ደረጄ