መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 17፤2015-ክፍቱን በተተወ ጉድጋድ ለውሃ ዋና የገባዉ የ25 ዓመት ወጣት ህይወቱ አለፈ

???? በዓመቱ በተመሳሳይ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል

ትላንት ማክሰኞ ማምሻዉን 11:30 ሰዓት ላይ በሸገር ከተማ ኮዬ ፈቼ ክፍለከተማ ልዪ ቦታዉ ቱሉዲምቱ አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተዉ ጉድጓድ ዉስጥ ከጓደኞቹ ጋር ዋና ለመዋኘት የገባዉ የ25 ዓመት ወጣት ህይወቱ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮምንኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን እንደተናገሩት የወጣቱ አስከሬን ለማግኘት ማምሻዉን ፍለጋ ቢካሄድም ሳይገኝ ቀርቶ ዛሬ እሮብ ነሀሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ማለዳ 3:00 ሰዓት ላይ የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች አስከሬኑን አግኝተዉ ለፖሊሰ አስረክበዋል።

በአዲስ አበባና አካባቢዋ ተቆፍረዉ ክፍቱን በተተዉና ዉሀ በአቆሩ ጉድጉዶች ዉስጥ ዋና ለመዋኘት እየገቡ ህይወታቸዉን የሚያጡ ታዳጊዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል።

የዛሬዉን የሞት አደጋ ጨምሮ በ2015 ዓ.ም በመሰል አደጋዎች ህይወታቸዉን ያጡ ታዳጊዎችና ወጣቶች ቁጥር 15 ሲሆን በጉዳዩ ላይ መፍትሄ መስጠት የሚገባቸዉ ተቋማትና ግለሰቦች የሰዉ ህይወት እየቀጠፈ ያለዉን ጉዳይ አሁንም ችላ እንዳሉት አቶ ንጋቱ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *