መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 18፤2015-በባሌ ዞን ለስራ ከተቀጠረበት ቤት ውስጥ ስምንት ሱሪ የዘረፈው ግለሰብ በ5 ዓመት እስራት ተቀጣ

በባሌ ዞን አዳርሳ ወረዳ ተከሳሽ ጀማል አህመድ የተባለው ግለሰብ ነሀሴ 12 ቀን 2015ዓ.ም በአንድ ግለሰብ ቤት በመግባ ለእርሻ ቦታ ጥበቃነት ከተቀጠረበት ቤት በመጀመሪያው ቀን ስምንት ጅንስ ሱሪዎችን መስረቁን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ስርቆቱን ከፈፀመ በኃላም ወደ አርሲ ሲራራ ወረዳ ሲያቀና በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮምኒኬሽን እና ሚዲያ ባለሞያ ዋና ሳጅን ጎሳ ተስፋየሁ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

ተከሳሹ አንድ ግለሰብ  ቤት በመግባት የተለያዩ  ስምንት ሱሪዎችን የሰረቀው በግለሰቡ ቤት ለስራ በተቀጠረ በአንደኛዉ ቀን መሆኑ አስቀድሞ ታስቦበት የተደረገ ወንጀል መሆኑን አክለዉ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በግለሰቡ ላይ በአፋጣኝ የምርመራ መዝገቡ በመክፈት እና  በማጣራት ለዓቃቢ ህግ ይልካል ።

ዓቃቢ ህግም መዝገቡን አደራጅቶ ዞን ሲናና ወረዳ ፍርድ ቤት በመላኩ ፍርድ ቤት የላከ ሲሆን በአንድ ቀን የምርመራ መዝገቡ ተጣርቶ ለባሌ ዞን ሲናና ወረዳ ተልኳል።ወረዳው ተከሳሽ ጀማል አህመድ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ5ዓመት ከ6ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ዋና ሳጅን ጎሳ ተስፋየሁ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

በምህረት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *