
በዛሬው እለት ነሀሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 መገናኛ መክሊት ህንጻ አካባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2_64440 የሆነ ቪትስ ተሽከርካሪ መንገድ ጥሶ ከባቡር ሀዳድ ዉስጥ መግባቱን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
በአደጋዉ ዕድሜዉ 25 የተገመተ አሽከርካሪዉ ህይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።
የኮሚሽን መስሪያ ቤቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወቱ ያለፈዉን አሽካርካሪ ከተሽከርካሪ ዉስጥ በማዉጣት እንዲሁም ሀዲድ ዉስጥ ገብቶ መንገድ የዘጋዉን ተሽከርካሪ በማንሳት የባቡር ሀዲዱን ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ተሽካርካሪዉ ከሀዲዱ ለማንሳት በነበረዉ ሂደት የባቡር አገልግሎት ለአንድ ሰዓት ያህል ተቋርጦ እንደነበር ለማወቅ ብስራት ራዲዮና ቲቪ ሰምቷል።
በትግስት ላቀው