መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 19፤2015-በኢራን ወራሽ የሌላቸው ጥንዶች ንብረታቸውን ለውሻቸው አስተላለፉ

ኢራናዊ ነጋዴ በእስር ቤት እንዲቆይ ያስገደደውን ድርጊት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ፈፅሟል። ባልተለመደ መልኩ የንብረት ዝውውር ከባለቤቱ ጋር ሲያደርግ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል።በጥንዶቹ የተፈረመውን ወረቀት ሲያዘጋጅ የነበረው የኢራን የንብረት ኤጀንሲ ኃላፊ  ቼስተር ለሚባለው ውሻ የንብረት ባለቤትነት የምስክር ወረቀት በመስጠቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ጥንዶቹ ልክ እንደ ሰው የውሻው ፊርማ በማስፈለጉ የእግሩን አሻራ ወረቀት ላይ ሲያስፈርሙ ታይተዋል። የንብረት ባለቤትነት መብት ዝውውሩን የሚያሳይ ምስል በኢራን ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ በስፋት ተሰራጭቷል። የንብረት ባለቤትነት መብት ዝውውሩን የሚመራው ኤጀንሲ ኃላፊ የህብረተሰቡን የሞራል እሴቶች ላይ ጥሰት በማድረግ እና የንብረት ስምምነቱን ፈቅዷል በሚል በቁጥጥር ስር ውሏል።

ንብረትን ለውሻ ማዘዋወር ህጋዊ መሰረት  የለውም ሲሉ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሬዛ ታባር ተናግረዋል ።የቴህራን ከተማ ምክር ቤት እንስሳትን እንደ ዋና ችግር በመግለጽ በሕዝባዊ ቦታዎች እንዳይገኙ ከልክለዋል። የኢራን ባለስልጣናት የግለሰቦችን ውሾች በተደጋጋሚ ይወርሳሉ።

ዶ/ር ፓያም ሞኸብ የኢራን ፓርላማ አባል ሲሆኑ ሁሉንም ውሾች በመውረስ ለእንስሳት ማቆያ እንዲሰጡ ወይም በበረሃ ውስጥ እንዲቆዩ የሚያስችል ህግ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *