መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 22፤2015-በአሜሪካ ሶስት ሰዎችን ተኩሶ የገደለው ግለሰብ በጥቁር ጥላቻ የዘረኝነት ድርጊት መሆኑ ተገለፀ

በፍሎሪዳ ዘርን መሰረት ባደረገ የጥላቻ ጥቃት ሶስት ሰዎችን በጥይት ተኩሶ የገደለው ግለሰብ ለጥቁሮች ያለውን ጥላቻ ያሰፈረበትን ጽሁፍ አግኝቻለሁ ሲል ፖሊስ አስታወቀ። የሃያ አንድ ዓመቱ ሪያን ክሪስቶፈር ፓልሜትር በጃክሰንቪል መኪናዋ ውስጥ ተቀምጣ የነበረች ሴት ላይ 11 ጊዜ ከተኮሰባት በኃላ ወደ ሱቅ በመግባት ሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ተኩሷል።

በስተመጨረሻም ሽጉጡን በራሱ ላይ እንዳዞረ ተናግሯል። ከንቲባ ዶና ዴጋን በዘረኝነት ጥላቻ የተመራ “በጥላቻ የተሞላ ወንጀል” ነው ብለዋል። እሁድ እለት በተደረገው የዜና ኮንፈረንስ ላይ፣ ገዳዩ ዋተር ፓልሜትር ከዚህ ቀደም የወንጀል ታሪክ እንደሌለው እና ከወላጆቹ ጋር በክሌይ ካውንቲ እንደሚኖሩ ተገልጿል።

ፓልሜትር ለጥቁሮች ያለውን ጥላቻ በዝርዝር ለወላጆቹ፣ ለመገናኛ ብዙሃን እና ለፌደራል ወኪሎች በርካታ መረጃዎችንን አዘጋጅቶ ነበር ሲል ፖሊስ ተናግሯል። “ይህ ተኩስ በዘር ላይ የተመሰረተ እና ጥቁር ሰዎችን ይጠላ እንደነበር” ማሳያ ሆኗል።

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ እንደተናገሩት የፍትህ ዲፓርትመንቱ “ይህን ጥቃት የጥላቻ ወንጀል እና ዘርን መሰረት ያደረገ የአመፅ ተግባር መሆኑን መርምሯል” ብለዋል። “በአሜሪካ ውስጥ ማንም ሰው በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን በመፍራት መኖር የለበትም እና የትኛውም ቤተሰብ የሚወዱትን ሰው በጭፍን ጥላቻ መነጠቅ የለባቸውም” ሲሉ አክለዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *