መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 23፤2015-በቅናት መንፈስ ለገንፎ የተጣደ የፈላ ውሃ በ16 ዓመት ታዳጊ ላይ የደፋች ግለሰብ በእስራት ተቀጣች

በኦሮሚያ ክል ባሌ ዞን ጎባ ከተማ ከባለቤቴ ጋር ያልተገባ ቅርበት ፈጥራለች በሚል ለገንፎ መስሪያ የተጣደ የፈላ ውሀን በ16 ዓመት ታዳጊ ወጣት ላይ በመድፋት የአካል ጉዳት ያደረሰችዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቷን የጎባ ከተማ ፖሊስ ገልጿል።

የጎባ ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤት ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንፔክተር ጎአ አማን ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን እንደገለፁት በባሌ ዞን ጎባ ከተማ ውስጥ ወ/ሮ እታለማሁ ደሞ የተባለች ግለሰብ ወልዳ አራስ ቤት ተኝታ እያለች እሷን ለማረስ የመጣችውን የ16 ዓመቷን ታዳጊ ከባለቤቴ ጋር ያልተገባ ግንኙነት ፈጥራለች በሚል ጥርጣሬ እና ቅናት ለገንፎ መስሪያ የተጣደ የፈላ ውሀ ሰውነቷ ላይ በማፍሰስ ከባድ ጉዳት አድርሳባታለች።

ተከሳሻ አራስ ቤት ሆና ለጎረቤቶቿ ገንፎ እንዲገነፉ በሰጠችው ትዕዛዝ የ16ዓመቷ ልጅ ውሀውን ጥዳ ተከሳሽም ገንፎው እንዴት እንደሚሰራ እያሳየቻት እንዳለ በተፈጠረ አለመግባባት ተከሳሽ እታለማው የፈላ ውሃውን አንስታ እንዳፈሰሰችባት ተናግረዋል።ተጎጂዋ የደረሰባትን ጉዳት ተከትሎ በጎባ ወረዳ ሆስፒታል የህክምና ክትትል አድርጋለች፡፡

ፖሊስ በድርጊቱ ፈፃሚ ላይ ባደረገው ምርመራ መዝገቡን አጣርቶ ለአቃቢ ህግ የላከ ሲሆን አቃቢ ህግም የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ክስ በመመስረት ለጎባ ወረዳ ፍርድ ቤት በመላኩ የጎባ ወረዳ  ከፍተኛ  ፍርድ ቤት  ተከሳሽ እታለማው ደሞ በፈፀመችው ወንጀል በ2ዓመት ከ3 ወር እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን  የጎባ ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤት ወንጀል ምርመራ ክፍል ሀላፊ ኢንፔክተር ጎአ አማን ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን ገልፀዋል።

በምህረት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *