መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 23፤2015-ከተወለደበት ሆስፒታል የተሰረቀው ሰው ከ42 ዓመታት በኋላ ከእናቱ ጋር ተገናኘ

በቺሊ ዋና ከተማ ሳንቲያጎ በሆስፒታል ሰራተኞች የተሰረቀው አሜሪካዊ ከ42 አመታት በኋላ ከወላጅ እናቱ ጋር ተገናኝቷል።

“ሆላ፣ እማማ” እያለ ጂሚ ሊፐርት ታይደን ከወላጅ እናቱ ጋር ሲነጋገርና ሰላምታ ሲለዋወጥ ታይቷል።ከአርባ ሁለት ዓመታት በፊት የሆስፒታል ሰራተኞች የማሪያ አንጀሊካ ጎንዛሌዝ ልጅ ከተወለደ በኋላ ከእቅፏ ይወስዳሉ ትንሽ ቆይተው በመምጣት መሞቱን ይነግሯታል።

አሁን ጎንዛሌዝ በቺሊ ቫልዲቪያ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከልጇ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተዋል። “በጣም እወድሻለሁ” በማለት ትይደን ሲያለቅስ ታይቷል።እንዴት ሰውን ለ 42 ዓመታት ማቀፍ በሚያስችል ሁኔታ ማቀፍ ይቻል?” ይሆን ሲል ጠይቋል።የማያውቀውን የትውልድ ቤተሰቡን የማግኘት ጉዞ የጀመረው ይህ ሰው በሚያዝያ ወር ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖስ ቡስካሞስ የተባለው የቺሊ ኩባንያ የጠፉ ሰዎችን ማገናኘቱን የሚገልፅ ዜና ካነበበ በኋላ ነው።

ድርጅቱ ታይደን በሳንቲያጎ በሚገኝ ሆስፒታል ያለጊዜው እንደተወለደ እና በማሞቂያ ክፍል ውስጥ መቀመጡን አረጋግጧል። ጎንዛሌዝ በጊዜው ከሆስፒታል እንድትወጣ የተነገራት ነገር ግን ዳግም ልጇን ለመውሰድ ስትመለስ፣ መሞቱንና መቀበሩን  ተነግሯታል።

የታይደን  የዘረመል ምርመራ 100 በመቶ ቺሊያዊ መሆኑንና ቤተሰቡን እንዲቀላቀል አስችሏል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *