መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 24፤2015-በጋቦን የጦር መኮንኖች በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን መቆጣጠራቸውን አስታወቁ

የሀገሪቱ የጦር መኮንኖች በጋቦን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ስልጣን እንደተቆጣጠሩ ተናግረዋል።

ቅዳሜ በተካሄደው ምርጫ ፕሬዚደንት አሊ ቦንጎ አሸንፈዋል የተባሉበትን የምርጫ ውጤት መሰረዙንም ገልፀዋል የምርጫ ኮሚሽኑ ቦንጎ ያሸነፉት ሁለት ሶስተኛው ድምጽ ብቻ በመያዝ ነው ሲል ያስታወቀ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ  ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ ተከራክረዋል። የአሊ ቦንጎ ከስልጣን መነሳት ለ53 አመታት በስልጣን የቆየወን የአንድ ቤተሰብ አስተዳደር እንዲያበቃ ያደርጋል።

ጋቦን ከአፍሪካ ዋና ዘይት አምራች ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን 90 በመቶ የሚጠጋው የአገሪቱ ክፍል በደን የተሸፈነ ነው። ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ላይ 12 ወታደሮች በብሄራዊ ቴሌቭዥን ቀርበው የምርጫውን ውጤት መሰረዛቸውን እና “የሪፐብሊኩን ሁሉንም ተቋማት” መበተናቸውን አስታውቀዋል።

የሀገሪቱ ድንበሮች ተጨማሪ መረጃ እስኪሰጥ ድረስ ተዘግተው እንደሚቆዩ ገልፀዋል።የጋቦንን ጨምሮ ባለፉት ሶስት አመታት በአፍሪካ በቀድሞ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ውስጥ ይህ ስምንተኛው መፈንቅለ መንግስት ይሆናል።

ወታደሮቹ ከሽግግር እና ተቋማቱ መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ የተውጣጡ እና በሀገሪቱ ያለውን የጸጥታና የመከላከያ ሰራዊት የሚወክሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከወታደሮቹ አንዱ በጋቦን የቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ “አሁን ያለውን አገዛዝ በማስወገድ ሰላምን ለመጠበቅ ወስነናል” ብሏል። ይህ ባይሆን አሁን ያለው አስተዳድር “ኃላፊነት የጎደለው፣ ሊተነበይ የማይችል  በቀጣይነት ያለው የማህበራዊ ትስስር መበላሸት ሀገሪቱን ወደ ትርምስ የመምራት አደጋን የሚያስከትል” መሆኑንም አክለዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *