
የአቃቂ ወንዝ በድንገተኛ ጎርፍ መሙላቱን ተከትሎ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በመውደቃቸው በአንዳንድ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት እንዲቋረጥ ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል ።
የሃይል አቅርቦት በገላን ኮንዶሚኒየም በከፊል እና በገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ ልዩ ቦታዉ ጫላ የከብት እርባታ እንዲሁም ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን በአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አ/ቶ መላኩ ታዬ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
አካባቢውም አስቸጋሪ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የሃይል አቅርቦቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ባለሙያዎች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
በአበረ ስሜነህ