መደበኛ ያልሆነ

ጳጉሜ 1፤2015-ለመጪው የዘመን መለወጫ በአል 5 ሺህ የእርድ እንስሳት እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታወቀ

ድርጅቱ ይህንን ያለው ለአዲስ አመት በአል የሚደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

በድርጅቱ የመረጃና ህዝብ ግንኙነት አገልግሎት ሃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረ ሚካኤል ለብስራት ሬዲዮና ቲቪ እንደተናገሩት በዘንድሮው የዘመን መለወጫ በአል እስከ 5 ሺህ የሚደርሱ የእርድ እንስሳቶች ይገባሉ ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ከእነዚህም መካከል 3 ሺህ ትላልቅ ወይም በሬ እና 2 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ትናንሽ ማለትም በግና ፍየል እንደሆነ ገልፀዋል።

ከአመራር ጀምሮ እስከ ታች ባለው የአሰራር ሂደት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አቶ አታክልቲ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ከዚህ ቀደም ያጋጥም የነበረውን የስርጭት መዘግየትችግር ለመቅረፍም 45 የሚሆኑ ዘመናዊ መኪኖች ከወዲሁ መዘጋጀታቸውን የህዝብ ግንኑነት ሃላፊው አስረድተዋል፡፡ 

በሌላ በኩል አዲስ አበባ በህገወጥ እርድ  የተነሳ በዓመት 1.53 ቢሊዮን ብር እንደምታጣ የቄራዎች ድርጅት አስታውቋል፡፡በተለይም የአካባቢ ብክለትን በማስከተል ለብዙዎች የጤና እክልን የሚፈጥር ጉዳይ እየሆነ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በአዲስ አበባ እየጨመረ የመጣውን ህገወጥ እርድን ለማስቀረት ከደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ጋር በመሆን የተለያዩ የቁጥጥር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡በሌላ በኩል  ህገወጥ እርድን የመከላከል ስራ የአንድ ተቋም ሃላፊነት ባለመሆኑ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን  በባለቤትነት ይህንን ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በቅድስት ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *