መደበኛ ያልሆነ

ጳጉሜ 3፤2015-በህገወጥ መንገድ ሊዟዟር የነበረ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ተያዘ !!

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በጥናት ላይ በመመስረት ክትትል ሲያድርግ ቆይቶ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሀሰተኛ ገንዘቦችን እያተሙ የሚያሰራጩ ሁለት ኢትዮጵያውያንና ሁለት የውጭ ሀገራት ዜጎችን  በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን ቀጥሏል።

በተሠራው ምርመራ የማስፋት ስራ መምሪያ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትእዛዝ በማውጣት ባደረገው ፍተሻ በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ አጃምባ የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ ባደረገው ብርበራ በህገወጥ መንገድ ሊዘዋወር የነበረ ከ1ሚሊዮን 7መቶ ሺ ብር በላይ ፣ መቶ የአሜሪካ ዶለር : በህትመት ሒደት ያለ በርከት ያለ ሀሰተኛ ብርን  ጨምሮ የተለየዩ የአፍሪካ ሀገራት ገንዘቦች፣ የፎቶ ካሜራ፣ የሞባይል ስልኮች፣ የነዋሪነት መታወቂያ ፣ የባንክ ATM ፣ ላፕቶፕ ፣ ፓስፖርት፣ የባንክ ሒሳብ ደብተር፣ የእጅ ግለቭና የመድሀኒት መርፌዎችን መያዙ ታውቋል፡፡

ከእነዚህ ኤግዚቢቶች በተጨማሪ ሀሰተኛ ገንዘብ ለማዘጋጀት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ተይዟል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎች ብርን እናባዘል በሚል ምክንያት ማሳሳቻ ዘዴን በመጠቀም ከግለሰቦች ላይ ገንዘብን ሲቀበሉ እንደነበር በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሀተሰኛ የገንዘብ ስርጭት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀሉን አስቀድሞ ለመከላከል ብሎም ወንጀለኞቹን ህግ ፊት ለማቅረብ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ስለሆነም።

ህብረተሰቡም ሆነ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት ጥቆማ የመስጠት ባህላቸውን አጠናከረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ መልእክት ተላልፏል፡

ምንጭ :- አ.አ ፖሊስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *