መደበኛ ያልሆነ

ጳጉሜ 3፤2015-ፓስፖርት ለማግኘት የሚጠባበቁ ከ 300 ሺህ በላይ ሰዎች መኖራቸውን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አሳወቀ

???????? ባለፉት 90 ቀናት ዉስጥ የፓስፖርት ቀጠሮአቸው ያለፋቸዉ ሰዎች ዘወትር ቅዳሜ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ አመራር ከተሾመለት ወዲህ ላለፈዉ አንድ ወር ያከናወነዉን የማሻሻያ ስራ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በዛሬዉ እለት ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአሁኑ ሰዓት በአገልግሎቱ ፓስፖርት ለማግኘት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ከ 300 ሺህ በላይ ዜጎች መኖራቸዉን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲሷ ዳይሬክተር ፤ ላለፈዉ አንድ ወር በተቋማቸዉ አሉ ያሏቸዉን ችግሮች ለመቅረፍ ምልከታ ማድረጋቸዉን ተናግረዋል።

በዚህም ተቋሙ የአጭር ፣ መካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅድ ነድፎ እየሰራ ነዉ ብለዋል። በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የሚነሳዉን እና ዜጎችን ያማረረዉ የሌብነት እና ብልሹ አሰራር ለመቅረፍ አዲስ የአሰራር መንገድ በመዘርጋት ላይ መሆኑን ገልጸዋል። በርከት ባሉ የተቋሙ ዳይሬክተሮች ፣ ሰራተኞች  እና በጊቢዉ ዙሪያ ባሉ ማስረጃ በተገኘባቸዉ ደላሎች ላይ ከአስተዳደራዊ እስከ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የተከሰተዉን ከፍ ያለ የፓስፖርት እጥረት ለመቅረፍ በዉጪ ከሚገኝ አምራች ተቋም ጋር ከስምምነት መድረሳቸዉን ጠቅሰዋል። ለእጥረቱ የዉጪ ምንዛሬ እጥረት እና አለማቀፍ ምክኒያቶች መንስኤ ነበሩ ብለዋል። ችግሩ አሁን በመጠኑ በመቀረፉ 190 ሺህ አዲስ ፓስፖርት ማተም መቻሉን ገልጸዉ ፤ አንገብጋቢ ለሆኑ ጉዳዮች ማለትም በአረቡ አለም ለሚገኙና በተለያዩ የዉጪ ሀገራት ካለ ፓስፖርት ለሚኖሩ ዜጎች ቅድሚያ መሰጠቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ባለፉት 90 ቀናት ዉስጥ የፓስፖርት ቀጠሮአቸው በተለያዩ ምክኒያቶች ያለፋቸዉ ሰዎች ዘወትር ቅዳሜ አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል። ወደ ኢትዮጵያ  ከዉጭ በሚመጡ ሰዎች ላይም ቪዛ ለማግኘት በነበረዉ ሂደት ይፈጸም ነበር ያሉትን ሌብነት ለመቀነስ ዘመናዊ አሰራር ተዘርግቷል ነዉ ያሉት። ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ሰዓትም ወዲያዉኑ ቪዛ የሚያገኙበትን On Arrival Visa ከመስከረም 15 ቀን ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል ብለዋል።

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፤ የቀጠሮ መያዣ ስርዓቱ የመሳስሎ ተሰርቶ ለደላሎች እና ሌቦች ተጋልጦ የነበረ መሆኑን ፣ አሰራሩ ዘመኑን ያልዋጀ እና ኋላ ቀር የነበረ መሆኑን ፣ እነዚህና ሌሎች ጥቃቅን ችግሮችን በተደራራቢነት የሚያመጡ ክፍተቶች ነበሩበት መባሉን ብስራት ሬዲዮና ቲቪ ዘግቧል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *