መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 4፤2016-በአዲስ አበባ ትላንት በጣለው ዝናብ የሁለት ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ

በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት ማምሻውን የጣለው ዝናብ በቦሌ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 12 ዳርፉር ወንዝ አካባቢ ከሚኖሩ ሰዎች   መካከል ሁለት ሴቶች በጎርፍ እንዲወሰዱ ማድረጉን   የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት  በጎርፍ ከተወሰዱት ሁለት ሴቶች ውስጥ እድሜዋ 18 ዓመት የሆነችዉ የአንደኛዋ አስከሬን ዛሬ ጠዋት 2:30 ሰዓት  በ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጥቁር አባይ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዉስጥ ተገኝቷል ።

የቀሪዋ ወጣት አስከሬን እየተፈለገ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *