መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 6፤2016-በዲማ ወረዳ ፆታውን በመቀየር በመስተንግዶ የተቀጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን  በዲማ ወረዳ ዲማ ከተማ በዛሬው ዕለት መስከረም 6 ቀን 2016 ዓ.ም ፆታውን በመቀየር በመስተንግዶ የተቀጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል ።

ግለሰቡ የአራት ዓመት ልምድ እንዳለው በመናገር ስሙን እና አለባበሱን የሴት በማድረግ በሆቴል መስተንግዶ ተቀጥሮ ለሁለት ቀናት ከቆየ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የዲማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት አ/ቶ ኡመድ ኦቶው ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ግለሰቡ ቢንያም ከበደ የሚባል ሲሆን ስሙን እና አለባበሱን ለመለየት በሚያዳግት መልኩ ሴት በመምሰል  በደላላ አማካኝነት ቃልኪዳን ወርቁ ተብሎ ገረመው ሆቴል የተቀጠረ ሲሆን  መነሻውን ጂማ ከተማ በማድረግ ወደ ከተማዋ የገባ መሆኑን አክለዋል ።

በዚህም ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውሎፕ ፆታው ወንድ እንደሆነ የተረጋገጠ ሲሆን ለምን እንደዚህ ማድረግ እንደፈለገ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ተገልጿል ።

በአበረ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *