
በዩጂን በተደረገ የዳይመንድ ሊግ የፍፃሜ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የ5,000ሜ የዓለም ሪከርድን በመስበር አሸንፋለች።
14:00.21 በሆነ ሰዓት የገባችው ጉዳፍ ፀጋይ የዓለም ሪከርዱን ከኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን በመንጠቅ ሪከርዱን የግሏ ማድረግ ችላለች።
” ትኩረቴ የነበረው የዓለም ሪከርዱን መስበር ነበር ” ያለችው ጉዳፍ በተመዘገበው ድል በጣም ደስተኛ መሆኗን እና በቀጣይ ከአስራ አራት ደቂቃ በታች ለመግባት እንደምትጥር ከድሉ በኋላ ተናግራለች።