መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 8፤2016-ህንድ ከፍተኛ የካናዳ ዲፕሎማትን ከሀገሯ አባረረች

የህንድ ተገንጣይ መሪ ግድያ ላይ የኒው ዴሊህ መንግስት እጅ አለበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ተናግረዋል።የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በሰኔ ወር በብሪቲሽ ኮሎምቢያ ውስጥ የካናዳ ህንድ ዜግነት ያለው ሃርዲፕ ሲንግ ኒጃርን በህንድ መንግስት ስለመገደሉ መረጃዎች ያሳያሉ ሲሉ ገልፀዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በኃላ በህንድ እና በካናዳ መካከል ያለው ግንኙነት ውጥረተ ነግሶበታል። ህንድ ክሱን “የማይረባ” እና ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ብላ ገልጻለች።

ካናዳ የህንድ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑትን ፓቫን ኩማርን ራይን ከሀገሯ አባራለች። በአፀፋው ህንድም አንድ ከፍተኛ የካናዳ ዲፕሎማትንም አስወጥታለች። ብሪታንያ ስለ ከባድ የግድያው ውንጀላ ከካናዳ ጋር በቅርብ እንደምትገናኝ ተናግራለች።

ዩናይትድ ስቴትስ ጉዳዩ በጣም እንዳሳሰባት ገልጻ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቃለች። የኒጃር ልጅ ባልራጅ ኒጃር በትሩዶ ንግግር እንደተገረመ ተናግሯል ምክንያቱም ከተኩስ በኋላ በነበሩት ሶስት ወራት ውስጥ “ምንም እንዳልተደረገ” እና የካናዳ መንግስት ዝምታን መምረጡን አስታውቋል።

የካናዳ የዓለም የሲክ ድርጅት ግድያውን አውግዞ ህንድ በምርመራ ላይ ከካናዳ መንግስት ጋር እንድትተባበር ጠይቋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *