መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 15፤2016-በቻይና ለ16 ድርጅቶች በእኩል ሰዓት ስትሰራ የነበረች የሽያጭ ባለሙያ በቁጥጥር ስር ዋለች

ቻይናዊቷ ግለሰብ በአንድ ጊዜ ለ16 የተለያዩ ኩባንያዎች ተቀጥራ እንደምትሰራ ከታወቀ በኋላ በማጭበርበር ወንጀል ተከሳለች። ነገርግን ይህችው ሴት ለ16 ኩባንያዎች ትስራ እንጂ በአንዳቸውም ላይ የስራ ገብታ ተገኝታ አታውቅም።

የቻይና መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ጓን ዩ የተባለችው ይህችው ሴት፣ ከደርዘን በላይ አሰሪዎችን ስታታል እና ቢያንስ ለሶስት አመታት ደሞዝ ስትሰበስብ ብትቆይም ለአንዳቸውም ምንም አይነት ስራ ሰርታ ግን አታውቅም ተብሏል። በዚህ ክስ የተጠረጠረው ባለቤቷ በቁጥጥር ስር ውሏል።በእያንዳንዱ ኩባንያ ውስጥ ያላትን ትክክለኛ ሚና፣ ለእያንዳንዳቸው መስራት የጀመረችበትን ቀን እና የባንክ ሂሳብ ዝርዝር ወርሃዊ ደሞዝ ፖሊስ እጅ ላይ ወድቋል።

ጓን ዩ ያለማቋረጥ አዳዲስ ስራ ትፈልግ እንደነበር ታውቋል። ወደ አዲስ የስራ ቃለ መጠይቆች ስትሄድ፣ ከደንበኞቿ ጋር ለመገናኘ እንደሄደች በማስመሰል ለሁሉም አሰሪዎቿ ፎቶዎችን አንስታ ትልክ ነበር። ማጭበርበሩ ለዓመታት ያለምንም እንከን ሰርቷል። በዚህም ጓን ዩ በሻንጋይ ከተማ ውስጥ ውድ አፓርታማ ቤት እንድትገዛ አስችሏታል።

ጓን ዩ በተለያዩ ድርጅቶች ስራን ለማግኘት በምታደርገው የማያቋርጥ ፍለጋ በጣም የተጠመደች በመሆኗ በርካታ የስራ ቃለ መጠይቆች በተመሳሳይ ጊዜ ታደርግ ነበር። አንዳንዴ ሲደራረብባት በኮሚሽን ስራውን ለሌሎች ሰዎች ታስተላልፍ ነበር። በውጤት ማጣት ከአንዱ ኩባንያ ስትባረር ሌላ ለመጨመር ስትደክም ትውላለች።ይህው ድርጊቷ ሊደረስበት የቻለው የስራ መልቀቂያን ደብዳቤ በአንዱ ድርጅት ስም ስማ ለሌላው በመላኳ ጉዳዩ ፖሊስ ዘንድ ደርሶ በቁጥጥር ስር ውላለች።

የሊዩ ጂያን ቢያንስ ለሶስት አመታት በነበረው የማጭበርበር ሂደት ከ50 ሚሊዮን ዩዋን በላይ ገንዘብ ሰብስባለች። አስገራሚው ነገር ጉዋን ዩ በቁጥጥር ስር ስትውል ቃለ መጠይቁ ስታደርግ ነበር። በተያዘችበት ጊዜ 16 ስራዎች ነበሯት ግን ለአንዳቸውም ምንም አይነት ትክክለኛ ስራ አልሰራችምግን ወርሃዊ ደሞዝ ታገኝ ነበር፣ እንዲሁም ስራ እንዲቀጠሩ ከረዳቻቸው አጋሮቿ ኮሚሽን ትቀበል ነበር።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *