መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 23፤2016-የካናዳ የፓርላማ አባላት የመጀመሪያውን ጥቁር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤን መረጡ

ካናዳ የሊበራል ፓርቲ አባል ግሬግ ፈርገስን አዲሱን የምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አድርጋ የመረጠች ሲሆን የቀደመው አፈ ጉባኤ በናዚ የፓርላማ ውዝግብ የተነሳ ከስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው። ፈርጉስ የስልጣን ቦታውን በመያዝ የመጀመሪያው ጥቁር ሰው ሆኗል።

338 አባላት ባለው ምክር ቤት ምርጫው ትላንት ምሽት በሚስጥር ድምፅ ከተሰጠ በኋላ አሸናፊው ተለይቷል። ለዚህ ሚና በመመረጤ “ትልቅ ክብር” ይሰማኛል ብሏል። የቀድሞው አፈ ጉባኤ ለናዚ የተዋጋውን ዩክሬናዊ ሰው ወደ ፓርላማ በመጋበዛቸው ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። የቀድሞ አፈ ጉባኤ አንቶኒ ሮታ  ንግግር እንዲያደርጉ የጋበዟቸው ሰው ከናዚ ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው አላውቅም ነበር ሲሉ አስታውቀዋል።

የቀድሞ አፈ ጉባኤውን ለመተካት ሰባት እጩዎች ተወዳድረው ነበር። በመጀመርያ ንግግራቸው፣ ፈርጉስ ባልደረቦቻቸው በምክር ቤቱ ውስጥ እርስበርስ በአክብሮት እንዲስተናገዱ አሳስበዋቸዋል፣ ይህ ቦታ “የፍቅር ክርክር” ነው። ‹‹ፖለቲካ የተከበረ ሙያ መሆኑን እናሳያቸዋለን ሲሉ አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጥቁር ካናዳዊ ለምክር ቤት አፈጉባኤነት መመረጣቸውን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ “ለመላው ካናዳውያን በተለይም በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ ለሚፈልጉ ወጣት ትውልዶች አበረታች መሆን አለበት” ብለዋል። ሹመቱን ግን አንዳንድ የወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ተቃውመዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *