መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 27፤2016-ለሐዘን በድንኳን ዉስጥ በነበሩ ሰዎች ላይ መንገዱን ጥሶ የመጣ አዉቶብስ ባደረሰዉ የትራፊክ አደጋ ሶስት ሰዎች ሞቱ

???????? የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ ይችላል ተብሏል

ትናንት ቅዳሜ መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት አለምፀሀይ ድልድይ አካባቢ አንድ የከተማ አዉቶቢስ ለለቅሶ የተደኮነ ድንኳን ጥሶ በመግባት በሐዘንተኞች ላይ ከሞት እስከ የአካል ጉዳት ማድረሱን የአዲስአበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

አቶ ንጋቱ እስከትናንት ምሽት ድረስ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከሀያ በላይ ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዉናል።

በድንኳኑ ዉስጥ የባለቤትዋን ለቅሶ የተቀመችዉ ግለሰብ ፤ በዚሁ አደጋ ወላጅ እናቷንም አጥታለች ያሉን አቶ ንጋቱ ፤ ሌሎች ህይወታቸዉን ያጡና ጉዳት የደረሰባቸዉም ሰዎች ሀዘንተኛዋን ለማጽናናት በድንኳን ዉስጥ የተቀመጡ ነበሩ ተብሏል።

በአደጋዉ ጉዳት  ከደረሰባቸዉ ተጎጂዎች መካከል የተወሰኑትን የኮሚሽኑ የቅድመ ሆስፒታልና አምቡላንስ አገልግሎት ባለሞያዎች ህክምና እያደረጉላቸዉ ወደ-ሆስፒታል አድርሰዋቸዋል ሲሉ ነግረውናል።

ጉዳት ከደረሰባቸዉ ዉስጥ በአስጊ ሁኔታ የሚገኙ ሰዎች እንዳሉ የተናገሩት አቶ ንጋቱ የሟቾች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በአጋዉ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአቤትና በራስ ደስታ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝም የአዲስአበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ጨምረው ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *