መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 30፤2016 – በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ነጮች ቁጥር መቀነሱን የህዝብ ቆጠራ አመላከተ

እኤአ በ2022 በተደረገው የደቡብ አፍሪካ የህዝብ ቆጠራ ውጤት የደቡብ አፍሪካ ህዝብ በ2011 ከነበረበት 51.7 ሚሊዮን ወደ 62 ሚሊዮን ደርሷል።ይህም ማለት በአማካይ በየዓመቱ የደቡብ አፍሪካ ህዝብ በአንድ ሚሊዮ እንደሚጨምር ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

በህዝብ ቆጠራው ማረጋገጥ እንደተቻለው በሀገሪቱ ውስጥ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች እንዳሉ አሳይቷል። ይህም ከጠቅላላው ህዝብ 3 በመቶ ገደማ ነው።

ወደ ደቡብ አፍሪካ ከሚሰደዱ ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ ከጎረቤት ሀገራት የመጡ ናቸው። 45.5 በመቶ ከዚምባብዌ፣ 18.7 በመቶ ከሞዛምቢክ እና 10.2 በመቶ ከሌሴቶ የመጡ ናቸው። በሌላ በኩል በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ነጮችን በተመለከተ እ.ኤ.አ በ1996 ከነበረበት 11 በመቶ የነጮች ህዝብ በ2022 ወደ 7.3 በመቶ ዝቅ ማለቱን ስታቲስቲክሱ ያሳያል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *