መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 2፤2016 –1.1 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን በ 24 ሰዓታት ዉስጥ ሰሜናዊ ጋዛን እንዲለቅቁ እስራኤል አሳሰበች

ሰባተኛ ቀኑን በያዘዉ የ ፍልስጤም – እስራኤል ጦርነት እስራኤል ከፍተኛ አጸፋዊ እርምጃን በፍልስጥኤም ላይ በመዉሰድ ላይ ትገኛለች።

እስራኤል በሀገሪቱ ላይ ከምታዘንበዉ ጥይት ጎን ለጎን የዉሃ ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የምግብ አቅርቦትን በጋዛ በማቋረጥ 2.5 ሚሊዮን ሰዎችን አደጋ ላይ ጥላለች።

እስራኤል አወጣች በተባለዉ ማሳሰቢያ በሰሜናዊ ጋዛ የሚኖሩ 1.1 ሚሊዮን ሰዎች በአፋጣኝ ወደ ደቡባዊ የጋዛ ክፍል በ 24 ሰዓታት ዉስጥ ለቅቀዉ እንዲጓዙ አዝዛለች ተብሏል። ይህም እስራኤል እወስደዋለሁ ባለችዉ የእግረኛ ወታደሮች ዘመቻ ጉዳት እንዳይደርስባችሁ ነዉ ብላለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ ይህን መሰል የጅምላ ዝዉዉር የማይቻል ሲል የጠቀሰዉ ሲሆን ሐማስ ሀሰተኛ የእስራኤል ማስጠንቀቂያ በመጠቀም የዉሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነዉ ብሎታል።

የኢራን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቤሩት በነበራቸው ቆይታቸዉ እንደተናገሩት ፤ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ያለችዉ የአየር ጥቃት ከቀለ በሌላ ግንባር ዉጊያ ሊከፈት እንደሚችል ጠቁመዋል። ይህም ጦርነቱ በአጎራባች ሀገራት ተሳትፎ ሊቀጥል እንደሚችል አመላክቷል።

እስካሁን እስራኤል በፈጸመችዉ ጥቃት 1 ሺህ 537 ፍልስጤማውያን መገደላቸው የተዘገበ ሲሆን 6 ሺህ 6 መቶ በላይ የሆኑ ሰዎችም ቆስለዋል ተብሏል። በእስራኤል በኩልም ሐማስ በፈጸመዉ ጥቃት 1 ሺህ 300 ሰዎች መገደላቸዉ ተዘግቧል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *