መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 26፤2016 – በሆንግ ኮንግ ፤ የኢትዮጵያ አየርመንገድን በመጠቀም በሰዉነቱ ዉስጥ አደንዛዥ እፅ ለማሳለፍ የሞከረዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከዩጋንዳ ኢንቴቤ በአዲስአበባ አድርጎ ወደ ሆንግ ኮንግ ባቀናዉ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ተሳፋሪ የነበረ ግለሰብ በሰዉነት አካሉ ዉስጥ አደንዛዥ እጽ ደብቆ ለማዘዋወር ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል።

ግለሰቡ የ 48 አመት ጎልማሳ ሲሆን በሰዉነቱ አካል ዉስጥ 1 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ እፅን በቀዶ ጥገና አስገብቶ ደብቆ ለማሳለፍ መሞከሩ ተዘግቧል።

በሆንግ ኮንግ አየር ማረፊያ በነበረ ፍተሻ ግለሰቡ መያዙ የተዘገበ ሲሆን በሰዉነቱ ዉስጥ እጹን መያዙ ሲረጋገጥ ወዲያዉኑ ወደ ህክምና ተቋም መወሰዱ ተገልጿል። እጹንም በዉስጡ ደብቆ ለማሳለፍ መሞከሩ በህክምና ዉጤት የተረጋገጠ መሆኑ ተነግሯል።

የግለሰቡ ዜግነት ያልተጠቀሰ ሲሆን  1 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ 68 የኮኬይን እንክብሎችን በሰዉነቱ ዉስጥ ይዞ መገኘቱ የተዘገበ ሲሆን በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀርቧል ተብሏል። ከሰሞኑ በተደጋጋሚ በሲሪላንካ በህጻናት የተረት መጽሃፍት ዉስጥ እና በናይጄሪያም የኢትዮጵያ አየርመንገድን በመጠቀም በተለያዩ መንገዶች እጽ ለማዘዋወር የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል።

በበረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *