መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 28፤2016 –በ30 ደቂቃ ውስጥ ሃንግኦቨርን የሚያጠፋው እና ሰውነት ውስጥ ያለውን የአልኮል መጠን በግማሽ የሚቀንሰው ተዓምራዊ መጠጥ መነጋገሪያ ሆኗል

ሴፍቲ  ሻት ወይም ለደህንነት መጎንጨት የሚል አቻ ትርጓሜ የተሰጠው ይህው አልኮል በዚህ አመት መጨረሻ ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን  ከአንድ ሰአት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በደም ውስጥ ያለውን የአልኮሆል መጠን ይቀንሳል።

ይህው መጠጥ የዞረ ድምር ውጤት (hangover) ን ታሪክ እንደሚያደርገው አምራቾቹ ቃል ገብተዋል። የዚሁ መጠጥ የገበያ ድርሻ በ2030 ዓመት ከ6 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ እንደሚሆን ባለሙያዎች ተንብየዋል።የአለም አቀፍ የሃንግኦቨር አስወጋጅ መጠን ፍላጎት እና ገበያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ፍጥነት እያደገ ይገኛል።

በዚሁ ዘርፍ ካሉ ተስፋ ሰጪ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ሴፍቲ ሻት ወይም በይፋዊ መጠሪያው ጁፒተር ዌልነስ ሲሆን ምርቱ በ 2023 ዓመት የመጨረሻ ወር ይጀምራል። በመጠጥ ገበያው ውስጥ ትልቁ አቅም ይፈጥራል የተባለው እና የመጠጥ ፈጠራ ቀመሩ ከወዲሁ አግራሞትን ፈጥሯል። የአንድን ሰው በደሙ ውስጥ ያለውን አልኮሆል ይዘት በ30 ደቂቃ ውስጥ ግማሹን በመቀነስ አጠቃላይ የጤንነት ስሜት እንዲሰማው እና በአልኮል የመመረዝ እድልን ይቀንሳል ተብሎለታል።

በሳይንስ የተረጋገጡ ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም የተፈጠረው ሴፍቲ ሻት የደም አልኮል መጠንን የሚሰብሩ ሜታቦሊዝም መንገዶችን በማጎልበት እና በጨጓራ አካባቢ የሚቀረውን አልኮሆል ወደ ሰውነት ውስጥ እንዳይገባ ለመከላከል የሚረዳ ነው ተብሏል። ተፈጥሯአዊ ቪታሚኖች እና ማዕድናት በመያዙ ሴፍቲ ሻት የደም አልኮል መጠንን ከማንኛውም ሌላ የሃንግኦቨር መድኃኒት በበለጠ ፍጥነት ይቀንሳል እንዲሁም የአእምሮን ብሩህነትን ያሳድጋል።

እንደ ኩባንያው ገለፃ ሴፍቲ ሻት በዚህ አመት በታህሳስ ወር በዩናይትድ ስቴትስ ገበያ ላይ የሚቀርብ ሲሆን በሌሎች ሀገራት ገበያ ውስጥ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል። ተአምረኛው መጠጥ በአንድ መለኪያ በአምስት የአሜሪካን ዶላር ለገበያ የቀረበ ሲሆን አራቱንጥቅል በ19.99 የአሜሪካን ዶላር ይሸጣል። መጠጡ በመጀመሪያ በአሜሪካ ውስጥ ባሉ ፋርማሲዎች ውስጥ እንደሚሸጥ ይጠበቃል።

ኩባንያዎች ለዓመታት የሃንግኦቨር መድሀኒት  ለማስተዋወቅ ሲሞክሩ ቆይተዋል፣። ከዚቢዮቲክ፣ በአለም የመጀመሪያው በዘረመል የተሻሻለው ፕሮቢዮቲክ፣ እስከ ከመጠጥ በኃላ በጠዋት ቶሎ ማገገሚያ እና ሀንግቨር የሌለው ቢራ ተጠቃሽ ናቸው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *