መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 28፤2016 –አንድ ወር ባስቆጠረው ጦርነት በጋዛ የሚገኙ ዳቦ ቤቶች በሙሉ ስራ ማቆማቸው ተነገረ

የጋዛ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በጋዛ ከተማ እና በሰሜን ጋዛ አካባቢዎች የሚገኙ ሁሉም ዳቦ መጋገሪያ ቤቶች በእስራኤል የቦምብ ድብደባ ፣ በነዳጅ እና በዱቄት እጥረት ሳቢያ ሥራ ማቆማቸውን አስታውቋል ። ባለፈው ወር መገባደጃ ላይ ኦክስፋም ለግዛቱ የሚሰጠውን የምግብ፣ የውሃ፣ የመብራት እና የነዳጅ አቅርቦት ካቋረጠ በኋላ እስራኤል ረሃብን “እንደ ጦር መሣሪያ” ተጠቅማለች ሲል ከሷል።

ከጥቅምት 21 ጀምሮ በአጠቃላይ 569 የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዛ ገብተዋል። ከጦርነቱ በፊት በየቀኑ የሚገቡት የጭነት መኪናዎች ቁጥር ከ750 እስከ 850 ይደርስ የነበረ ሲሆን ያለውን ሰብዓዉ ቀውስ በሚገባ እንደሚያሳይ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል በእስራኤል በትላንትናው እለት ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስከፊ የሆነውን ጥቃት ተከትሎ ተጎጂዎችን ለማሰብ የአንድ ደቂቃ ዝምታ ሰፍኖ ነበረ። ጥቃቱ ልክ ከአንድ ወር በፊት በትላንትናው እለት ያጋጠመ ነበር ። የሟቾች ቤተሰቦች ህዝቡ ጥቁር ሸሚዝ በመልበስ ብሄራዊ መዝሙር እንዲዘምሩ ጠይቀዋል።

በየትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች የመታሰቢያ ስነ-ስርአት በትላንትናው እለት ተካሂዷል። በተጨማሪም በጋዛ ታግተው የሚገኙ 240 የሚጠጉ ሰዎች ቤተሰቦች ዘመዶቻቸውን በሰላም ወደ ቤታቸው ለመመለስ የበለጠ ግፊት በማድረግ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *