መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 8፤2016 – በአሜሪካ አንዲት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰራተኛ ከ11 አመት ልጅ ጋር ፆታዊ ግንኙነት በመፈፀሟ ተከሰሰች

አንድ የቀድሞ የኮነቲከት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሰራተኛ በመኪናዋ ውስጥ በተደጋጋሚ  ከ11 አመት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽማለች በሚል ክስ በቁጥጥር ስር ውላለች። የ42 ዓመቷ አሊሰን ክራኒክ ከልጁ ጋር የተገናኘው በ2022 ሲሆን ልጁ በተደጋጋሚ ማታ ማታ ከቤት ሾልኮ በመውጣት ቢያንስ በተለያዩ ቀናት 14 ጊዜ ግንኙነት ፈፅመዋል።

የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ግለሰብ የ11 ዓመቱን ታዳጊ ከመውደዷ የተነሳ “BFFLWB” የሚል ምህጻረ ቃል ያለው የእጅ አምባር አድርጋለተለች። ትርጉሙም “ከጥቅ ጋር በህይወት ዘመን ምርጥ ጓደኛማቾች” እንደ ማለት ነው። ተከሳሿ ልጁን ከጠዋቱ 2 ሰዓት ብዙ ጊዜ ከቤቱ ታስወጠው ነበር። “ሁልጊዜ ደክሞት” ይመጣ የነበረ ሲሆን የኃይል መጠጦች በመስጠት እንዲነቃቃ ታደርገው እንደነበር ለመርማሪዎች ታዳጊው ተናግሯል።

በፎረንሲክ ቃለ መጠይቅ ወቅት እንደተረጋገጠው ልጁ ክራኒክ ከተባለችው የትምህርት ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኛ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንዲፈጽም “ታስገድደው” እንደነበር እናና “የጾታ ጥቃት እንደደረሰበት” ተናግሯል። ፖሊስ ክሬኒክን ከ400 በላይ የፅሁፍ መልዕክቶችን እንደላከችለት አስታውቋል።  ፖሊስ ታዳጊው ባልፈለገበት ጊዜ ከእርሷ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ እንደተገደደ ገልጿል።

በቤዛዊት አራጌ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *