መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 10፤2016 – በሳውዝ ካሮላይና አንዲት መምህር ከታዳጊ ልጅ ጋር ያልተገባ ግንኙነት ነበራት በሚል ተከሰዎች

???? ወላጆች ‘የልጃችንን ሕይወት አበላሽታለች’ ሲሉ ተናግረዋል

አንድ የቀድሞ የሳውዝ ካሮላይና መምህርት ከ17 ዓመቱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእግር ኳስ ተጫዋች ላይ ያልተገባ ግንኙነት በመፍጠሯ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአካባቢው የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የ27 ዓመቷ ባለትዳር የሁለት ልጆች እናት ሬገን አንደርሰን በሆሊ ሂል አካዳሚ ተማሪ ላይ ባደረሰችው በደል ሁለት የወሲብ ጥቃት የሚል ክስ ቀርቦባታል።

የተጎጂው እናት በፍርድ ቤት ቀርባ በሰጠችው ቃል እንደተናገረችው ታማኝ አሰልጣኝ፣ አስተማሪ እና ጓደኛ ብለን አደራ የሰጠናት አስተማሪ አደራውን ረስታ የልጃችንን ህይወት አበላሽታለች ብላለች። የእግር ኳስ ተጫዋች እና እግር ኳስን የሚወደው ታዳጊው ልጄ መቶ በመቶ ለእግር ኳስ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። ነገር ግን ይህንን ማድረግ እንዳይችል ተደርጓል ስትል እናት ክሷን አሰምታለች።

ይህች ሴት ነፃ ከወጣች በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ የትኛውም ወጣት ሯጭም ሆነ ስፖርተኛ ደህና ሆኖ አይቀጥልም ስትል የተበሳጨችው  እናት ገልፀዋል። የፍርድ ቤቱ ዳኛ አንደርሰንን በ2,500 ዶላር ዋስትና ከእስር ተለቃ የፍርድ ቤቱን ጉዳይ እንድትከታተል ውሳኔ አሳልፏል። ሆኖም ግን ከተጠቂው ሆኑ ከቤተሰቡ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳትፈጥር ፍርድ ቤቱ በማስጠንቀቅ ፤ የጂፒኤስ ሞኒተር ወይም ክትትል እንዲደረግባት ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የቀፍሞ አስተማሪዋ በቡች ፎርድ መንገድ ላይ እና ከፒዛ ሃት ተሽከርካሪ ማቆሚያ ስፍራ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ በመፈፀም በሚል ተከሳለች።በተጨማሪም አንደርሰን ታዳጊውን የእርቃን ፎቶግራፎች በስናፕ ቻት ላይ እንዲልክ እንዳስገደደችው ተገልጿል።

የሆሊ ሂሊ አካዳሚ በሰራተኛው እና በከፍተኛ ትምህርት ቤት ተማሪ መካከል ያለውን ተገቢ ያልሆነ ግንኙነት አስመልክቶ ውንጀላ የቀረበበት ሲሆን የትምህርት ቤቱ ኃላፊ ብራንዲ ሙሌናክስ ለወላጆች በላኩት ደብዳቤ መሰረት “አስተዳደሩ ወዲያውኑ የህግ አስከባሪ አካላትን አነጋግሯል.” ሲሉ ገልፀዋል። በመግለጫው አንደርሰን ከአሁን በኋላ በዚህ ትምህርት ቤቱ እንደማትሰራ እና አስተዳደሩ ከኦሬንጅበርግ ካውንቲ የፖሊስ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር እየሰራ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ ባለፎው ሳምንት በአሜሪካ አንዲት አንድ የቀድሞ የኮነቲከት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሰራተኛ በመኪናዋ ውስጥ በተደጋጋሚ  ከ11 አመት ልጅ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽማለች በሚል ክስ በቁጥጥር ስር መዋሏን መዘገባችን ይታወሳል። የ42 ዓመቷ አሊሰን ክራኒክ ከልጁ ጋር የተገናኘው በ2022 ሲሆን ልጁ በተደጋጋሚ ማታ ማታ ከቤት ሾልኮ በመውጣት ቢያንስ በተለያዩ ቀናት 14 ጊዜ ግንኙነት ፈፅመዋል።

የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ግለሰብ የ11 ዓመቱን ታዳጊ ከመውደዷ የተነሳ “BFFLWB” የሚል ምህጻረ ቃል ያለው የእጅ አምባር አድርጋለተለች። ትርጉሙም “ከጥቅም ጋር በህይወት ዘመን ምርጥ ጓደኛማቾች” እንደ ማለት ነው። ተከሳሿ ልጁን ከጠዋቱ 2 ሰዓት ብዙ ጊዜ ከቤቱ ታስወጠው ነበር። “ሁልጊዜ ደክሞት” ይመጣ የነበረ ሲሆን የኃይል መጠጦች በመስጠት እንዲነቃቃ ታደርገው እንደነበር ለመርማሪዎች ታዳጊው መናገሩን ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *