
???? ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት አስተላልፈዋል
በአርጀንቲና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሁለተኛ ዙር መደረጉን ተከትሎ የቀኝ ዘመም አክራሪ ብሄርተኛ ጃቪየር ሚሌይ በጊዜያዊው ውጤት መሰረት አሸንፈዋል። የሚሌ ተቀናቃኝ የኤኮኖሚ ሚኒስትሩ ሰርጂዮ ማሳ ውጤቱን እንደተቀበሉ ተናግረዋል። የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “አርጀንቲናን በድጋሚ ታላቅ እናደርጋለን!” በማለት ሚሌይን በማሸነፋቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ምርጫው እየጨመረ የመጣው የዋጋ ግሽበት እና በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ በገባችው አርጀንቲና በአስቸጋሪ ወቅት ላይ ተደርጓል። ማዕከላዊ ባንክን ጨምሮ ሚሌ የያዟቻው ሃሳቦች ለለውጥ ተስፋ ላደረጉ መራጮች ዘንድ ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል።ጊዜያዊ ውጤቶች እንዳሳዩት ሚሌይ 56 በመቶ የሚጠጋ ድምጽ ያገኙ ሲሆን ተቀናቃኛቸው ማሳ 44 በመቶ ድምፅ አግኝተዋል።እስካሁን 90 በመቶ የመራጮች ድምፅ ተቆጥሯል።
ሚሌይ ከድላቸው በኃላ ቦነስ አይረስ ከተማ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት የድል ንግግር “ዛሬ የአርጀንቲና ተሃድሶ ተጀምሯል ፤ ዛሬ የአርጀንቲና ውድቀት የማብቂያ ቀን ነው ሲሉ ተናግረዋል። አርጀንቲና በፍፁም ልታጣው ወደማይገባው በአለም ላይ ወደነበረችበት ቦታ ትመለሳለች ብለዋል። የተሸለ አለምን ለመገንባት ከሁሉም የነፃው አለም ሀገራት ጋር ትከሻ ለትከሻ እንሰራለን ብለዋል።
በምርጫው የተሸነፉት ተቀናቃኛቸው ማሳ በበኩላቸው “በእርግጥ ውጤቶቹ እኛ የጠበቅነው አይደሉም፤ ሃቪየር ሚሌይን አነጋግሬዋለሁ እንኳን ደስ ያለህ ብያለሁ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ከቀድሞው የብራዚል መሪ ጃየር ቦልሶናሮ ጃቪየር ጋር ሚሌይ ግንኙነት እንዳላቸው ግን አልተረጋገጠም።
የአሜሪካን ዶላር የሀገሪቱን መገበያያ ገንዘብ አድርጋለው ማለታቸው በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ጭብጨባ ቢያስከትልም በርካታ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ግን አደጋ እንዳለው እየተናገሩ ይገኛል። ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት ከ140 በመቶኛ በላይ በሆነበትና ከአምስት ሰዎች መካከል ሁለቱ በድህነት ውስጥ የሚኖሩባት አገር ከዚህ የከፋ ነገር አይመጣም ሲሉ ሌሎች ደግሞ ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ።
በስምኦን ደረጄ