በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የስነ ምግባር ጥሰት በታየባቸው 305 የወረዳ ፈፃሚዎች (ኦፊሰሮች) ላይ ከቀላል እስከ ከባድ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ይህን ያለው የ2016 አም የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክን ከሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በመሆን ባካሄደበት ወቅት ነው።በባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ምስራች ግርማ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከ305 ቱ የወረዳው ፈፃሚ ሰራተኞች መካከል አንዱ ከስራ እንዲባረር ተደርጓል።
አያይዘውም 283 የሚሆኑት በቀላል የስነምግባር ጥሰር 17ቱ ደግሞ በከባድ ቅጣት እንዲቀጡ ተደርጓል።በሩብ አመቱ የደንብ ጥሰት ታይቶባቸዋል ከተባሉት መካከል የ4ቱ አፊሰሮች ጉዳይ በፍርድ ቤት ተይዟልም።
ባለስልጣኑ ይህን ችግር ለመቅረፍ እና በቀጣይ የስነምግባር ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ ለማድረግ ለኦፊሰሮች ግንዛቤ የመፍጠር ስራን እንደሚያከናውን ገልጿል።
በቅድስት ደጀኔ