መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 10፤2016 – በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አስር ቀናት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ22 ሰዎች ህይወት አልፏል

በኦሮሚያ ክልል በ2016 ዓ.ም ከጥቅምት 28  እስከ ህዳር 8 ባሉት ቀናት አርባ አራት የትራፊክ አደጋዎች የ22 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋዎቹ ህይወታቸውን ካጡት ሰዎች መካከል አርባ አራት ሰዎች ላይ  ከባድ እና አስር  ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

አደጋዎቹ  በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎች የተከሰቱ መሆናቸውን ተጠቁሟል። ከደረሱት አደጋዎች መካከል ሁለቱ ብቻ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተመዝግቧል።

ከደረሱት አደጋዎች መካከል በምሰራቅ  ወለጋ ዞን  ጅጋ  ወረዳ  ልዩ ስሙ  ማጎ ተብሎ  የሚጠራው አካባቢ ህዳር 8 2016 ዓ.ም  ከጠዋቱ 4 ፡30 አካባቢ  የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 61871 የሆነ ዶልፊን ተሸከርካሪ ላይ የደረሰው አደጋ  የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ  ከባድ አካል ጉዳትምዳ ያጋጠመበት ጭምር መሆኑ ተነግሯል፡፡

የአደጋዎቹ  መንስኤዎቹ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣በቂ እረፍት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር እንዲሁም አሽከርካሪዎች እርስ በእርስ በመሽቀዳደም መሆኑን ኢንስፔክተር መሰለ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ኢንስፔክተሩ  አክለውም አሽከርካሪዎች  በፍጥነት፣ ጠጥተዉ እንዲሁም በመሽቀዳደም  የሰዉን  ህይወት  ከመቅጠፍ እንዲጠነቀቁ ሲያሳስቡ እግረኞችም በተቻላቸዉ አቅም ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ ራሳቸዉን ከትራፊክ አደጋ እንዲጠብቁ በአፅኖት አሳስበዋል።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *