???? በጋዛ የሟቾች ቁጥር ከ13 ሺ በልጧል
የእስራኤል ወታደራዊ ሃይል በጥቅምት 7 ከደረሰው የሃማስ አስከፊ ጥቃት በኋላ ታጋቾች ወደ ትልቁ የጋዛ ሆስፒታል ሲወሰዱ የሚያሳይ ምስል ነው ያለውን ቪዲዮ አጋርቷል። የወታደራዊ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ አንድ ወታደር እዚሁ ተገድላለች ሲሉ ገልፀዋል ። የ19 ዓመቷ ወታደር የተገደለችው ቀላል ጉዳት ደርሶባት ወደ አል-ሺፋ ሆስፒታል ከተወሰደች በኋላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
እስራኤል የሐማስ ማዘዣ ማዕከል ነው በምትለው አል ሺፋ ሆስፒታል ውስጥ ዋሻ ማግኘቱን ተናግራለች። ሃማስ ግን ይህንን መረጃ የሀሰት ሲል ያስተባብላል። የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት (አይዲኤፍ) እሁድ እለት በሰጠው የዜና መግለጫ ላይ የቀረበውን ቪዲዮ በተመለከተ ግን በገለልተኛ አካል ማረጋገጥ አልተቻለም።
ለኖኦን ቤተሰብ ህይወቷ እንዳለፈ አሳውቀናል ባደረግነው ቅኝት መሰረት ሺፋ አካባቢ ወደሚገኝ ደህንነቱ የተጠበቀ ቤት ታግታ ነበረ ሲሉ የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ሪየር አድም ዳንኤል ሃጋሪ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በአካባቢው የእስራኤል ጦር የአየር ጥቃት በፈፀመበት ወቅት ኖኦን የያዘው የሃማስ ታጣቂ ሲገደል እስራኤላዊቷ ወታደር በአየር ድብደባ ቆስላለች። ነገር ግን ለህይወቷ አስጊ የሆነ ጉዳት አልደረሰባት።
ኖህ ወደ ሺፋ ሆስፒታል ተወሰደች ነገር ግን በሌላ የሃማስ ታጣቂ ተገድላለች ብለዋል። ሃማስ ቀደም ሲል ኖህ ማርሲያኖ እስራኤል በፈፀመችው የአየር ጥቃት መገደሏን አስታውቆ ነበር።እስራኤል የኢንዶኔዥያ ሆስፒታል አካባቢን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን ኢላማ በማድረግ በጋዛ ላይ የምታደርገውን አደገኛ ጥቃት ቀጥላለች። የቦምብ ጥቃቱ ከጥቅምት 7 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ 13,000 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፈ ምክንያት ሆኗል።
በአብርሃም ፍቅሬ